ደብራችን


የኦስትሪያ ቪየና ደብረ ሲና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን


የኦስትሪያ ቪየና ደብረ ሲና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምዕራብ አዉሮፓ ሀገረ ስብከት ማዕከላዊ የአስተዳደር መዋቅር ስር የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን ናት። ቤተ ክርስቲያናችን ከተቋቋመችበት ጀምሮ በልዩ ልዩ ምክንያት ከሀገራቸው ወጥተው በኦስትሪያና አካባቢዋ ለሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ወንጌልን በማስተማርና ነገረ እግዚአብሔርን በማሳወቅ በመንፈሳዊና በማኅብራዊ ኑሯቸው እንዲበረቱ መንፈሳዊ ተልዕኮዋን በመወጣት ላይ ትገኛለች።

የኦስትሪያ ቪየና ደብረ ሲና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የእናት ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ፣ ቀኖና፣ ሥርዓትና ትውፊት ጠብቃ እዚህ ትልቅ ደረጃ መድረሷን በደስታ ስናበስር፤ ባለፍንባቸው የፈተና ዓመታት ሁሉ በምህረቱና በጥበቃው ላልተለየን ለአባቶቻችን አምላክ ከፍ ያለ ክብርና ምስጋና እናቀርባለን።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የኦስትሪያ ቪየና ደብረ ሲና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ስርአትን በመከተል የምታቀርበውን መንፈሳዊ አገልግሎት ተካፋይ እንድትሆኑ መንፈሳዊ ጥሪ ታደርጋለች።






ያግኙን


የአገልግሎት ሰዓት

ዘወትር እሁድ ከጠዋቱ 7:30 am ጀምሮ

አድራሻ

Wienerstrasse 18
2320 Schwechat
Österreich

ኢሜል

[email protected]







የባንክ አካውንት


Äthiopisch-Orthodoxe Tewahedo Kirche  der Debre Sina Kidist Kidane Mehret Kirche Wien

BANK: Bank Austria

IBAN: AT721200010024108663

BIC: BKAUATWW












ፎቶ ማህደር






መልዕክት ካሎት


error: Alert: Content is protected !!