አምስቱ አእማደ ምሥጢር
አዕማድ ቋሚ ፣ ተሸካሚ ፣ ምሰሶ ማለት ነው፡፡ ቤተክርስቲያንም የእምነት መሠረት የሆኑትን ትምህርቶች አዕማደ ምሥጢራት ትላቸዋለች፡፡ አዕማድ የተባሉት ልቦናን ከኑፋቄ ፣ ከጥርጥር የሚያድኑ ስለሆነ ነው፡፡ ምሰሶ የሌለው ቤት እንደሚወድቅ ሁሉ አዕማደ ምሥጢራትም ያላመነ ፣ ያላወቀ ሰው ቢኖር ይወድቃል፡፡
እነዚህም ምሥጢራት
– ምሥጢረ ሥላሴ (የሥላሴን አንድነትና ሶስትነት የምንማርበት)
– ምሥጢረ ሥጋዌ (የአምላክን ሰው መሆን… የምንማርበት)
– ምሥጢረ ጥምቀት (ስለ ዳግም መወለድ.. የምንማርበት )
– ምሥጢረ ቁርባን (ስለ ክርስቶስ ሥጋና ደም… የምንማርበት)
– ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን(ስለ ትንሣኤ ሙታን የምንማርበት) ናቸው ።
ምሥጢር
አመሠጠረ ከሚለው ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ስውር ፣ ድብቅ ፣ ሽሽግ ማለት ሲሆን አምስቱ አዕማደ ምሥጢራትም ምሥጢር የተባሉበት ምክንያት
- በፍጡር ጥበብና እውቀት ምርምር መረዳት ስለማይቻሉ
- ላመኑት እንጂ ላላመኑት ሰዎች የተሰወረ በመሆኑ
Recent Sermons
የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የአባልነት መመዝገቢያ ቅፅ
March 30, 2018
ቤተክርስቲያናችን እንደ ተቋም በሃገሩ ህግ የተመዘገበችበት
March 29, 2018
እግዚአብሔርን መፍራት
February 17, 2018