አምስቱ አእማደ ምሥጢር

አምስቱ አእማደ ምሥጢር

አዕማድ ቋሚ ፣ ተሸካሚ ፣ ምሰሶ ማለት ነው፡፡ ቤተክርስቲያንም የእምነት መሠረት የሆኑትን ትምህርቶች አዕማደ ምሥጢራት ትላቸዋለች፡፡ አዕማድ የተባሉት ልቦናን ከኑፋቄ ፣ ከጥርጥር የሚያድኑ ስለሆነ ነው፡፡ ምሰሶ የሌለው ቤት እንደሚወድቅ ሁሉ አዕማደ ምሥጢራትም ያላመነ ፣ ያላወቀ ሰው ቢኖር ይወድቃል፡፡

እነዚህም ምሥጢራት
– ምሥጢረ ሥላሴ (የሥላሴን አንድነትና ሶስትነት የምንማርበት)
– ምሥጢረ ሥጋዌ (የአምላክን ሰው መሆን… የምንማርበት)
– ምሥጢረ ጥምቀት (ስለ ዳግም መወለድ.. የምንማርበት )
– ምሥጢረ ቁርባን (ስለ ክርስቶስ ሥጋና ደም… የምንማርበት)
– ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን(ስለ ዳግም ምጽዓት የምንማርበት) ናቸው ።

በአፈፃፀማቸው መሰረት በሶስት ይከፈላሉ ።
. ምሥጢረ ሥላሴና ምሥጢረ ሥጋዌ አምነን የምንቀበላቸው ።
. ምሥጢረ ጥምቀትና ምሥጢረ ቁርባን አምነን በሥራ ::
. ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን አምነን በተስፋ የምንጠብቀው ።

በዘመናት አከፋፈላቸው በሶስት ይከፈላሉ ።
. ምሥጢረ ሥላሴ ቅድመ ዓለም ከዘመናት በፊት ያለውን
. ምሥጢረ ሥጋዌ
. ምሥጢረ ጥምቀት
. ምሥጢረ ቁርባን በዘመነ ሥጋዌ የሆነውን
. ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ከዓለም ፍጻሜ በኋላ የሚሆነውን ያስረዳሉ ።

ምሥጢር መባላቸው ስለምንድን ነው

ምሥጢር

አመሠጠረ ከሚለው ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ስውር ፣ ድብቅ ፣ ሽሽግ ማለት ሲሆን አምስቱ አዕማደ ምሥጢራትም ምሥጢር የተባሉበት ምክንያት

  • በሥጋው ጥበብ ምርምር መረዳት ስለማይቻሉ
  • ላመኑት እንጂ ላላመኑት ሰዎች የተሰወሩ በመሆኑ

ምሥጢር በሁለት ይከፈላል፡፡ እነርሱም፡-

የፈጣሪ ምሥጢር፡- ሊገለጥ የማይችል ነው፡፡ ከ እስከ የሌለው ምሥጢርም ይባላል፡፡

የፍጡራን ምሥጢር፡- በጊዜ የሚገለጥ /የሚታወቅ/ ነው፡፡ የሰውና የመላእክት ምሥጢር በዚህ ውስጥ የሚካተት ነው፡፡

 

share

error: Alert: Content is protected !!