አምስቱ አእማደ ምሥጢር

አምስቱ አእማደ ምሥጢር

አዕማድ ቋሚ ፣ ተሸካሚ ፣ ምሰሶ ማለት ነው፡፡ ቤተክርስቲያንም የእምነት መሠረት የሆኑትን ትምህርቶች አዕማደ ምሥጢራት ትላቸዋለች፡፡ አዕማድ የተባሉት ልቦናን ከኑፋቄ ፣ ከጥርጥር የሚያድኑ ስለሆነ ነው፡፡ ምሰሶ የሌለው ቤት እንደሚወድቅ ሁሉ አዕማደ ምሥጢራትም ያላመነ ፣ ያላወቀ ሰው ቢኖር ይወድቃል፡፡

እነዚህም ምሥጢራት
– ምሥጢረ ሥላሴ (የሥላሴን አንድነትና ሶስትነት የምንማርበት)
– ምሥጢረ ሥጋዌ (የአምላክን ሰው መሆን… የምንማርበት)
– ምሥጢረ ጥምቀት (ስለ ዳግም መወለድ.. የምንማርበት )
– ምሥጢረ ቁርባን (ስለ ክርስቶስ ሥጋና ደም… የምንማርበት)
– ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን(ስለ ትንሣኤ ሙታን የምንማርበት) ናቸው ።

 

ምሥጢር

አመሠጠረ ከሚለው ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ስውር ፣ ድብቅ ፣ ሽሽግ ማለት ሲሆን አምስቱ አዕማደ ምሥጢራትም ምሥጢር የተባሉበት ምክንያት

  • በፍጡር ጥበብና እውቀት ምርምር መረዳት ስለማይቻሉ
  • ላመኑት እንጂ ላላመኑት ሰዎች የተሰወረ በመሆኑ

 

Share

error: Alert: Content is protected !!