በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::


ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!!!



እንኳን ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ድኅረ ገፅ በሰላም መጡ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የኦስትሪያ ቪየና ደብረ ሲና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ስርአትን በመከተል የምታቀርበውን መንፈሳዊ አገልግሎት ተካፋይ እንድትሆኑ መንፈሳዊ ጥሪ ታደርጋለች።

ቤተ ክርስቲያናችን ከተቋቋመችበት ጀምሮ በልዩ ልዩ ምክንያት ከሀገራቸው ወጥተው በኦስትሪያና አካባቢዋ ለሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ወንጌልን በማስተማርና ነገረ እግዚአብሔርን በማሳወቅ በመንፈሳዊና በማኅብራዊ ኑሯቸው እንዲበረቱ መንፈሳዊ ተልዕኮዋን በመወጣት ላይ ትገኛለች።

የኦስትሪያ ቪየና ደብረ ሲና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የእናት ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ፣ ቀኖና፣ ሥርዓትና ትውፊት ጠብቃ እዚህ ትልቅ ደረጃ መድረሷን በደስታ ስናበስር፤ ባለፍንባቸው የፈተና ዓመታት ሁሉ በምህረቱና በጥበቃው ላልተለየን ለአባቶቻችን አምላክ ከፍ ያለ ክብርና ምስጋና እናቀርባለን።

የአገልግሎት ሰዓት

ዘወትር እሁድ ከጠዋቱ 7:30 am ጀምሮ

አድራሻ

Wienerstrasse 18
2320 Schwechat
Österreich

ኢሜል

[email protected]





ራዕያችን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትና ሥርዓት በኦስትሪያና አካባቢዋ ተስፋፍቶና ተጠናክሮ ማየት፡፡

ምእመናን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ቀኖና እና አስተምህሮ እንዲያውቁ ማድረግ፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን አንዲት ቅድስትና ዓለማቀፋዊት እንደመሆኗ መጠን ይህንኑ ማንነቷን በማጽናት እና አገልግልቷን በማጠናከር ለትውልድ ማሰተላስፍ፡፡

በአጥቢያው የሚገኙ ወጣቶች እና ሕፃናት በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ እምነት እና ሥርዓት የሚሄዱ ሆነው በእውቀታቸው፣ በገንዘባቸው፣ በጉልበታቸው ሲያገለግሉ እና በመንፈሳዊ ዕውቀት ጎልምሰው በክርስቲያናዊ ሕይወት ሲኖሩ ማየት፡፡






ተልዕኳችን

የቤተ ክርስቲያናችንን የአገልግሎት አድማስ በማስፋት ምእመናን በቃለ እግዘአብሔር ታንጸው ሃይማኖታቸዉን አጽንተዉ ፈጣሪያችዉን በመማጸን የንሰሓ ፍሬ አፍርተዉ የእግዚአብሔር በረከተ ተሳታፊዎች እንዲሆኑና የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዲወርሱ ማድረግ፡፡

ሕፃናትን በቋንቋ፣ በሃይማኖት እና በክርስቲያናዊ ስነ ምግባር ማነጽ፡፡

ከአጥቢያው ቤተክርስቲያን በተጨማሪ አቅም በፈቀደ መጠን ገዳማት፣ አድባራትን እና የአብነት ትምህርት ቤቶችን በመርዳት ቅድስት ቤተክርስቲያንን መጠበቅ እና አገልግሎቷም የተሟላ እንዲሆን ማገዝ፤ ዕጓለ ማውታ ሕፃናትን ረዳት አልባ  አረጋውያንን የሚረዱ መንፈሳዊ ተቋማትን ማገዝ፡፡

የእግዚአብሔርን ወንጌለ መንግሥት ለማኀበረ ምእመናን በማስተማር የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑን አባላት በትምህርተ ወንጌል ማነጽ፡፡





THERE IS NO UPCOMING EVENT NOW!





April 06, 2017

አምስቱ አእማደ ምሥጢር

አምስቱ አእማደ ምሥጢር

አዕማድ ቋሚ ፣ ተሸካሚ ፣ ምሰሶ ማለት ነው፡፡ ቤተክርስቲያንም የእምነት መሠረት የሆኑትን ትምህርቶች አዕማደ ምሥጢራት ትላቸዋለች፡፡ አዕማድ የተባሉት ልቦናን ከኑፋቄ ፣ ከጥርጥር የሚያድኑ ስለሆነ ነው፡፡







April 21, 2017

ሰንበት ት/ቤት

ሰንበት ት/ቤት

የሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የጾታ ልዩነት ሳይደረግ መንፈሳዊ ወጣቶችን  በዕለተ ሰንበት: በዓበይት በዓላትና አመቺ በሆነ ጊዜ ሁሉ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እየተገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን







March 27, 2017

ኪዳነ ምሕረት

ኪዳነ ምሕረት

ኪዳን የሚለው ቃል ‹‹ቃል›› ከሚለው ጋር እየተዛረፈ በብሉይ ኪዳን ለ280 ጊዜ ያህል ሲጠቀስ በአዲሰ ኪዳን ደግሞ ከ32 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ ‹‹ኪዳን›› ቃሉ ‹‹ተካየደ›› ተማማለ፣ ቃል ተገባባ ከሚለው...








መሰረተ እምነት



24
Apr

አምስቱ አእማደ ምሥጢር

አዕማድ ቋሚ ፣ ተሸካሚ ፣ ምሰሶ ማለት ነው፡፡ ቤተክርስቲያንም የእምነት መሠረት የሆኑትን ትምህርቶች አዕማደ ምሥጢራት...

Read More




የቅርብ መርሐ ግብራት



error: Alert: Content is protected !!